መስከረም 26/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ለ25ኛ ጊዜ በተካሄደው የጽንስና የማህጸን ሐኪሞች ዓለም አቀፍ ፌደሬሽን (FIGO) ዓለም አቀፍ ኮንግረስ ላይ፤ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የሴቶችን ጤና በማሻሻል ላበረከቱት አስተዋጽኦ የ2025 FIGO ተሸላሚ ሆነዋል።

Post image

ዶ/ር መቅድስ በቨርቿል መልእክታቸው፤ በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶችን ጤና በማሳደግ ረገድ ለሚደረገው የጋራ ሥራ እውቅና ስለተሰጣቸው አመስግነዋል።

Post image

ይህ ሽልማት ለእርሳቸው ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ ላሉ ሴቶች እና የቤተሰባቸውን ጤና፣ ክብር እና ደህንነት ለማሻሻል ሕይወታቸውን ለሚሰጡ ሁሉ መሆኑን ገልጸዋል።

25ኛው የጽንስና የማህጸን ሐኪሞች ዓለም አቀፍ ፌደሬሽን (FIGO) ዓለም አቀፍ ኮንግረስ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ኮንግረሱ በማህፀን ሕክምና እና በማህፀን ሕክምና መስክ የሳይንስ እና ሳይንሳዊ ምርምር እድገትን ለማሳደግ በዓለም አቀፍም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ አስተዋፅኦ ላደረጉ ሴቶች እውቅና ይሰጣል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ