ሕዳር 26/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከማርበርግ ቫይረስ ምልክቶች ታይተውባት፤ በለይቶ ማቆያ የሕክምና ክትትል ሲደረግላት የቆየች ታካሚ ከማርበርግ ቫይረስ በሽታ ነፃ መሆኗ ተገልጿል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ አራተኛዋ ሰው ከማርበርግ ቫይረስ በሽታ ታክማ ነፃ ሆና ወደ ቤተሰቦቿ መቀላቀሏን ገልጸዋል።

Post image

ታካሚዋ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምልክቶችን አይታ በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም መምጣቷ ለመዳኗ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቁመው፤ የሕክምና ማዕከሉ ጤና ባለሙያዎች ያደረጉትን ትጋትና ርብርብ ማመስገናቸውን ጤና ሚኒስቴር ለአሐዱ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ