መስከረም 29/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን "በድንገተኛ አደጋዎችና ሰብዓዊ ቀውስ ወቅት የአእምሮ ጤና አገልግሎት ተደራሽነት" በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ተከብሯል።

ዓለም አቀፋዊ የአዕምሮ ጤና ቀን አስመልክቶ አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት፣ ሲቪል ማህበራትና የማህበረሰብ አደረጃጀቶች የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች ነው ዕለቱ የተከበረው።

በመድረኩም የተለያዩ ዝግጅቶች የተደረጉ ሲሆን፤ የፓናል ውይይት የአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሀኪሞችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ባለሙያዎች ጋር የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

Post image

በዚህም በተለይም በድንገተኛ አደጋዎችና ሰብዓዊ ቀውስ ወቅት ያለው የአዕምሮ ሕክምና አገልግሎት ያለበት ደረጃ ያሉ ክፍተቶች ላይ ውይይት ተደርጓል።

እንዲሁም የግንዛቤ፣ ቅድመ መከላከል ሥራዎች፣ የበጀት ምደባ በድንገተኛ አደጋዎች ላይ፣ የገቢ ምንጭ አማራጮች የባለሙያዎች ወደሌላ ዘርፍ መቀየር የሚስተዋል መሆኑን በዝግጅቱ ከተገኙ ተሳታፊዎች የተነሱ ሀሳቦች ናቸው።

የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34 ጊዜ በኢትዮጵያ ለ12 ጊዜ የሚከበር መሆኑም ተገልጿል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ