መስከረም 19/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ እና ጣሊያን በሽሬ እና በጎንደር ሆስፒታሎች የጤና አጠባበቅ አገልግሎትን ለማጠናከር የ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዩሮ ስምምነት መፈራረማቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስምምነቱን የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ ተፈራርመዋል።
ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በተለይም ግጭት፣ መፈናቀል እና የሕዝብ አገልግሎት መቋረጥ በሚስተዋልባቸው በትግራይ እና አማራ ክልሎች ላይ የፕሮጀክቱ መጀመር አስፈላጊነቱን አጽንዖት ሰጥተውበታል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
የሽሬ እና የጎንደር ሆስፒታሎችን ለማጠናከር የሚያስችል የ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዩሮ ስምምነት ተፈረመ
