ጥቅምት 25/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማሕበር በቀረበበት የዕቅበተ ዕምነት ጉዳይ ክስ ቀርቦበት ጉዳዩ ወደ ቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ ማሕበሩ ፈጸመ የተባለው የዶግማና ቀኖና ጥሰት እንዲጣራ ቋሚ ሲኖዶስ ሚያዝያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሠረት በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በማህበሩ ላይ የቀረበውን ክስ በጥልቀትና በስፋት አጥንተው የሚያቀርቡ ልዑካን ተመድበው ላለፉት ሁለት ወራት የልዑካኑ የማጣራት ሥራ መካሄዱ ተገልጿል፡፡
ይህም ለቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ ከታየ በኋላ፤ ቋሚ ሲኖዶስ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የልዑካኑን ማጣራት ተመልክቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጥሎበት የነበረው እግድ ከፍተኛ ማስጠንቀቅያ በመስጠት እንዲነሳ ወስኗል፡፡

በዚሁ መሠረት የማሕበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ መነሻ በማድረግ ከዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማሕበር ላይ ተላልፎ የነበረው በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ መነሳቱን የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ገልጿል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ