ጥቅምት 20/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ካፒታልን ከዕድል ጋር ለማገናኘት የተቋቋመ ኢንዲፔንዳንት የኢንቨስትመንት ባንክ የመሆን አላማን የያዘው ፈርስት አዲስ ኢንቨስትመንት ባንክ፤ 28 ሚሊዮን ብር ካፒታል በመበጀት በይፋ ሥራውን በዛሬው ዕለት በይፋ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ስድስት ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት ውስጥ አንዷ ናት ያለው ባንኩ፤ በአጠቃላይ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የንግድ ተቋማት እና ወደ 32 የሚጠጉ የንግድና የልማት ባንኮች አሏት ብሏል።

Post image

ሆኖም እንደ ሀገር በፋይናስ አገልግሎት ተደራሽነትም ሆነ በካፒታል ገበያ እድገት ገና ብዙ ይቀራታል ሲል ገልጿል።

ባንኩ በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ ሆቴል ለብዙሃን የመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ በይፋ ወደ ሥራ መግባቱን የገለጸ ሲሆን፤ ወደሥራ ሲገባ 28 ሚሊዮን ብር ካፒታል በመበጀት መሆኑን አስታውቋል።

ማህበረሰቡን ከመሰረታዊ የቁጠባ እና የብድር አገልግሎት ውጪ የተጨማሪ የፋይናስ አገልግሎቶች፣ ለምሳሌ የግለሰብ ኢንቨስትመንት አካውንቶች የመክፈት መጠቀም እድል አልነበረውም ሲል ያስታወሰው ባንኩ፤ ይህን ችግር ለመፍታት ሥራ መጀመሩን ገልጿል።

የካፒታል ገበያን ማስፋትና ማጠናከር የኢኮኖሚን ዕድገት ለማስቀጠል ብሎም የዜጎችን ተጠቃሚነት ከማስፋት አንፃር አስተማማኝ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽነት የሆነ የኳፒታል ገበያ አስፈላጊ ስርዓት ነው ሲልም ተደምጧል።

Post image

የባንኩ ዋናኛ ተልዕኮም፤ ፍላጎት ተኮር የኢንቨስትመንት መፍተሔዎችን ለግለሰቦች፣ ለድርጅቶች፣ እና ለመንግሥት በማቅረብ የካፒታል ተደራሽነት ማጎልበትና እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን ማምጣት ሲሆን፤ ራዕዩም በኢትዮጵያ ታማኝ የኢንቨስትመንት ባንክ አጋር መሆን ነው ሲል አስታውቋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ