ጥቅምት 18/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ቢሾፍቱ የሚገነባው አይሮፕላን ማረፊያ ዲዛይን ሥራ እንደተጠናቀቀ አስታውቀዋል፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላየይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ከአይሮፕላን ማረፊያው የዲዛይን መጠናቀቅ በተጨማሪም የኤርፖርቱ ግንባታ አማካሪም ተቀጥሯል ብለዋል፡፡

የሚገነባው ኤርፖርት ከ100 ሚሊየን ተሳፋሪዎችን የሚያስተናግድ በመሆኑ ከአፍረካ የመጀመሪያ ትልቅ ኤርፖርት እንደሚደርገው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ይህ ግዙፍ የ10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንትም ኢትዮጵያን በቀጣይነት የአፍሪካ የአቬሽን ማእከል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል ብለዋል፡፡

ኤርፖርቱ በሚገነባበት ቦታ ያሉ አርሶ አደሮች ኑሮአዋቸው ሳይሰተጓገል በተገቢው መልኩ መልሶ ለማቋቋም ሰፊ ሥራ ተሰርቷል ሲሉም አብራርተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም አርሶ አደሮች መሬታቸውን ሲለቁ የሚስተናገዱበት መንገድ ስህተት ነበረበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህን ለመቅረፍ ፕሮጀክቱ ሳይጀመር ሙሉ በሙሉ አርሶ አደሮች ደስተኛ ሆነው፣ ኑሮአቸው ተሻሽሎ ከወጡ፣ በአካባቢው የምንገነባው አየር መንገድ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያመጣል ብለዋል።

አክለውም፤ በቦሌ አየር መንገድ ከለውጥ በኋላ በርካታ የማስፍፊያ ሥራዎች ተሠርተዋል ያሉ ሲሆን፤ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን እንደሚያስተናግድ ገልጸዋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ