መስከረም 29/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ጊፍት ሪል እስቴት ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚቆይ ኤክስፖ፤ በ2 በመቶ ቅድመ ክፍያ እስከ 25 በመቶ ቅናሽ የተደረገባቸውን 1 ሺሕ 500 ቤቶች ለሽያጭ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡
ሪል እስቴቱ የ2018 ሁለተኛውን "መኖር በጊፍት መንደር" የሽያጭ ኤክስፖ መርሃ ግብር፤ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡

በዚህም የሽያጭ ኤክስፖ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ በመዲናዋ ግንባታ የጀመሩና በቀጣይ የሚገነቡ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለሕዝብ ይፋ አድርጓል።
ጊፍት ሪል እስቴት፣ ሦስት መንደሮችን ጨርሶ ለሕብረተሰቡ ባስረከበበት ማግስት፤ አራተኛውን የጊፍት ሜትሮፖሊታን መንደር፣ በከተማዋ በለገሀር ላይ 4 ሺሕ ቤቶችን በመገንባት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
ከእነዚህ መካከል 12 ሺሕ ቤቶች ማስፋፊያ አካል የሆኑ በሁለተኛና ሦስተኛ ዙሮች የሚገነቡ 8 ሺሕ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች እንዲሁም፤ 6 ኪሎ፣ በቦሌ መድኃኒዓለም፣ በፊጋ፣ በ22 ማዞሪያ፣ በተክለሃይማኖት፣ በሲኤምሲ እና በሌሎች አካባቢዎች በአጠቃላይ ከ16 ሺሕ በላይ ቤቶች ተዋውቀዋል።
ለኑሮ ምቹ በሆኑት መንደሮች ትምህርት ቤ/ቶች፣ የሕክምና ተቋማት፣ ሞሎች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች ከበቂ የመኪና ማቆሚያ ጋር ተካተዋል።
ጊፍት ሪል እስቴት በባለፈው 2017 ዓመት በተዘጋጀው የሽያጭ ኤክስፖ ከ2 ሺሕ 500 ቤቶች በላይ መሸጣቸው የገለጸ ሲሆን፤ በዚህም 10 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
እስካሁን ድረስም በ165 ሺሕ ካሬሜትር ላይ በሲኤምሲ እና ፈረስ ቤት ሦስት ትላልቅ መንደሮችን ገንብቶ ለማኅበረሰቡ በማስረከብ ችሏል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ