መስከረም 28/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይ.ሲ.ሲ) የጣሊያን ጠቅላይ ጆርጂያ ሜሎኒን ጨምሮ ሁለት ሚኒስትሮቻቸውን በጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተባባሪ ሆነዋል በሚል ክስ መስርቶባቸዋል።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ እንዳስታወቁት ከሆነ፤ እራሳቸውን ጨምሮ ሁለት ሚኒስትሮቻቸው በጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተባባሪ ሆነዋል በሚል ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተከሰናል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ በፍርድ ቤቱ ክስ የቀረበው እርሳቸውን ጨምሮ የመከላከያ ሚኒስትሩ ጊዶ ክሮሴቶ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ እና የጣሊያን መከላከያ ድርጅት ሊዮናርዶ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሮቤርቶ ሲንጎላኒ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የክሱን መረጃ ማን እንደናገራቸው ከመግለፅ የተቆጠቡት ሚሎኒ፤ ነገር ግን "በዓለም ላይ በታሪክም ቢሆን እንደዚህ አይነት ክስ አይቼም ሲምቼም አላቅም" ሲሉ ተናግረዋል።
"ምዕራብ እየሩሳሌም በሃማስ ላይ መጠነ ሰፊ የመሬትና የአየር ጥቃት ከፍታ ብትቆይም፤ ሮም ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ለእስራኤል አላቀረበችም" ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሯ ክሱን ማጣጣላቸውን አርቲ ኒዉስ ዘግቧል።
ሜሎኒ ለአይ.ሲ.ሲ "ክሱ በፖለቲካ ተቀናቃኞች የቀረበ ነው" ሲሉ ውድቅ አድርገው፤ እርሳቸውም ሆኑ ሚኒስትሮቻቸው በጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተባባሪ እንዳልሆኑ ተከራክረዋል።
ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ. በ2002 በሮም ስምምነት መሠረት የዘር ማጥፋትን፣ የጦር ወንጀሎችን እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን አጣርቶ ክስ ለመመስረት ተቀባይነት አግኝቷል።
እስካሁን 123 ሀገራት ስምምነቱን በማፅደቅ፤ የፍርድ ቤቱ ሙሉ አባላት ናቸው። ይሁን እንጂ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ አሜሪካ እና እስራኤልን ጨምሮ ታላላቅ የዓለም ኃያላን ሀገራት ስምምነቱን አልፈረሙም ወይም አላፀደቁትም።
ቀደም ሲል እስራኤልን ሲደግፍ የነበረዉ የጣሊያን መንግሥት፤ ጥቃቱን 'ተመጣጣኝ አይደለም' ሲል ነቅፎ በቅርቡ ራሱን አግልሏል።
አሁንም ጣሊያን ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊም ሆነ የንግድ ግንኙነት አላቋረጠችም። እንዲሁም ለፍልስጤም መንግሥትነት እውቅና ለመስጠት ከሌሎች ምዕራባውያን ሀገራት ጋር አልተባበረችም።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር በዘር ማጥፋት ወንጀል ተባባሪ ሆነዋል ሲል በአይሲሲ ክስ ቀረበባቸው
