መስከረም 28/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ አድርጓል።

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታችሁን ለምትከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የሪሜዲያል (Remedial) ፕሮግራም ምደባ በቅርቡ ይፋ የሚደረግ መሆኑንም አስታውቋል።

ምደባ ለመመልከት 👉Website: https://student.ethernet.edu.et

👉Telegram bot: @moestudentbot

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ