ጥቅምት 5/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ቀይ ባህር ከአፋር ክልል 60 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና በታሪክም የኢትዮጵያ አካል በመሆኑ የባህሩን ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ከፌደራል መንግሥት ጋር በመተባበር እንደሚሰራ የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለአሐዱ ገልጿል
የቢሮው ኃላፊ ሙሃመድ አሊ፤ "በታሪክ የኛ የነበረውን ቀይ ባህር ባለቤትነት በሰላማዊ መንገድ እና አስፈላጊውን መሰዋእትነት በመክፈል ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት ሀገር እንዳትሆን በትኩረት እንሰራለን" ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ለዘመናት የቀይ ባህር ባለቤት እንደሆነች የተለያዩ መረጃዎች እንዳሉና ቀይ ባህር ከኢትዮጵያ እጅ የወጣው ከ27 ዓመት በፊት መሆኑን አንስተው፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ለማስመለስ በሚያደርገው ጥረት ሁሉ የአፋር ሕዝብና መንግሥት ከጎኑ መሆኑን ገልጸዋል።
የአፋር ሕዝብ ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ኮሪደርን የምታገኝበት ኮሪዶር መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ የባህር በር ጥያቄው በአጭር እና በረጅም ጊዜ መሳካቱ አይቀርም ሲሉ ጠቁመዋል።
የባህር በር ጥያቄ ሀገራዊ አጀንዳ ከመሆን ባለፈ ዓለም አቀፋዊ አጀንዳ የተደረገበት ወቅት በመሆኑ፤ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለሀገር ጥቅም በመተባበር የኢትዮጵያ መንግሥት በወደብ ጉዳይ ላይ በሚያደርገው ጥረት ከጎኑ መቆም አለባቸው ሲሉም ተናግረዋል።
ሰላም ታስቀድማለች ድህነትን ትፋለማለች መውጫ መግቢያ በሯን ታበጃለች ይህ አይቀሬ ጉዳይ መሆኑን ተገንዘበው ወንድም እህቶቻችን በፈጠነ ጊዜ ለድርድር እራሳቸውን ዝግጁ ማድረግ አለባቸው
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በ80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕርና በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ለሚገኙ ሁሉም ሀገራት እኩል ልማትና ደህንነትን ለማረጋገጥ "ሁሉን አቀፍ አካሄድ" እንደምትከተል በመግለጽ፤ ሕጋዊ የፖሊሲ ግቧን በዲፕሎማሲያዊና በሰላማዊ ተሳትፎ እንደምታስቀጥል ለዓለም መንግሥታት ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡
በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ በ6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በአባይ ግድብና በቀይ ባህር እንደመገኘቷ፤ እጣ ፋንታዋ እና መፃኢ እድሏ ከሁለቱ ውሀዎች ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ሀገሪቱ ካላት ጂኦግራፊያዊ፣ ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ዳራ አንፃር የጋራ ልማትን ለማጠናከር ሰላማዊ ዕድሎችን የሚፈጥር በጋራ ጥቅም እና አጋርነት መርህ ላይ የተመሰረተ የባህር ዳርቻን የማረጋገጥ ውይይት መጀመሯን የገለጹት ፕሬዝዳንት ታዬ፤ ይህም አጀንዳ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ ትኩረት እየሳበ መምጣቱን መግለጻቸውም አይዘነጋም፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
የአፋር ክልል መንግሥት የቀይ ባህር ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ከፌደራል መንግሥት ጋር በመተባበር እንደሚሰራ አስታወቀ
