መስከረም 21/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ‎የዓለም የነዳጅ ዋጋን መነሻ በማድረግ ከዛሬ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በመስከረም ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ከዛሬ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ሥራ ላይ የሚውል የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን ይፋ አድርጓል።

Post image

በዚህም የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በመስከረም ወር ሲሸጥበት በነበረበት እንደሚቀጥል ገልጿል።

ነገር ግን የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሽጫ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ 120.10 ብር/በሊትር እንዲሆን በመንግሥት መወሰኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎችም በነዳጅ ምርቶች ግብይት አዋጁና በአሠራር መመሪያው መሠረት ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉም ማሳሰቢያ አስተላልፏል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ