በቀይ ባህር አካባቢ የሚኖሩ ከ300 ሺህ በላይ የአፋር ህዝብ በኤርትራ መንግስት አማካኝነት መፈናቀላቸውን የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አስታውቋል።

በኤርትራ መንግስት በአፋር ህዝብ ላይ የመብት ጥሰት መፈፀሙን የተናገሩት የድርጅቱ ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን ናቸው

ከእነዚህም ውስጥ የቀይ ባህር አፋር ህዝብ ከታሪካዊ መሬታቸው በህገወጥ መንገድ እንዲፈናቀሉ ማድረጉን እና ወደ ጎረቤት ና ሌሎችም ሀገራት መሰደዳቸውን ገልፀዋል።

ከተፈናቀሉት ባሻገርም በቋንቋ እንዳይማሩ ማድረግን ጨምሮ የቀይ ባህር አፋር ህዝብን ማንነትና ባህል የማጥፋት ስራ መሰራቱንም አንስተዋል።

ብዙ ወጣቶች፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች እንደሚሰደዱ ያነሱት ሊቀመንበሩ ካሉበት አካባቢ ሆን ተብሎ ለቀው እንዲወጡ ለማድረግም ምንም አይነት የልማት ስራ አለመኖሩን ገልፀዋል።

ድርጅቱ በትላንትናው እለት በሰጠው መግለጫ በኤርትራ መንግስት የዘር ማጥፋት ወንጀልን ጨምሮ ተፈፅሟል ላለው ሌሎች የመብት ጥሰቶች ለአፍሪካ ህዝባዊና ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያቀሰበውን ክስ አስመልክቶ ኮሚሽኑ በ60 ቀናት ውስጥ መልስ እንዲሰጥበት ለማድረግ ለኤርትራ መላኩን መግለፁ ይታወሳል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ