በትግራይ ክልል ህፃፅ መጠለያ ጣቢያ በሚገኙ በርካታ ተፈናቃዮች እየተባባሰ በመጣ የረሃብ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ።
በአስከፊ የምግብ እጥረትና በውስን የህክምና አገልግሎት ምክንያት ተደጋጋሚ ሞት እየተመዘገበ መሆኑንና በርካታ ሰዎች በአስከፊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ዘገባዎች ያመላክታሉ።
ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለው በህፃፅ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች በምግብና በመድሀኒት እጥረት ሰዎች እንዲሞቱ ምክንያት መሆኑ እየተገለፀም ይገኛል።
የሚቀርብላቸው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነና አልፎ አልፎ የሚሰጣቸው 15 ኪሎ ግራም እህል መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እንደማያሟላም ሲገልጉ ቆይተዋል።
ተፈናቃዮቹ እህሉን ለማስፈጨትና ለሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ወጪም ለመሸፈን ግማሹን እህል ለመሸጥ እንደሚገደዱ መግለፃቸዉን አሐዱም መዘገቡ ይታወሳል።
በተጨማሪም የሚቀርበው የእህል ዓይነት ለህጻናት ለአረጋውያንና ለታመሙ ሰዎች ለመመገብ አስቸጋሪ መሆኑን ሲገልፁም ቆይተዋል፡፡
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ሁሉም በሚባል ደረጃ መግለጫ በማዉጣት ተኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡
በምርጫ ቦርድ ዕዉቅና የተነፈገዉ ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይም በጉዳዩ ላይ መግለጫ ያወጣ ሲሆን ፌደራል መንግስትን ክፉኛ ወቅሷል።
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም በህፃፅ የተከሰተዉን ርሀብ መፍትሄ እንዲሰጠዉም ጥሪ አቅረበዋል።
ከፖርቲዎች መካከልም መግለጫ በማዉጣት ቀዳሚ የሆኑት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)ታህሳስ 13 ቀን ባወጣው መግለጫ ከጦርነት የተረፉ ንፁሀን በረሀብ እየተገረፉ መሆኑ ትልቅ የሰብዓዊነት ልሽቀት ነው ሲል ገልፃል።
ሌላኛው በጉዳዩ ላይ መግለጫ ያወጣው ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት) ሲሆን ፓርቲው በህፃፅ ያለውን የረሃብ ቀውስ ለመፍታት የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተዋናዮች አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
አሐዱም ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለዉ ያለፉትን አምስት ዓመታት በተለያዩ መጠለያ ጣብያዎች ኑሮቸዉን ያደረጉ ተፈናቃዮችን ጠይቋል።
ተፈናቃዮቹ ያለፉትን አምስት ዓመታት በከባድ ስቃይ ዉስጥ መቆየታቸዉን የገለፁ ሲሆን በህፃፅ የተፈጠረዉ ደሞ ከሁሉም የሚለይ መሆኑን ያነሳሉ።
የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበርም ሲጠየቅ የቆየ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ተግባራዊ አለመደረጉ አሁን ለተከሰተዉ ችግር መንስኤ መሆኑ ይገለፃል፡፡
በህፃፅ ጉዳይ መግለጫ ካዋጡ ፖርቲዎች መካከል አንዱ የሆነዉ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) በበኩሉ የተፈናቃዮች ስቃይ ለዘመናት የቆየው የህወሃት አገዛዝ መዋቅራዊ ውድቀት ውጤት መሆኑንና ይህም ክልሉን ለረሃብና ለእንግልት እንደዳረገው ገልፃል፡፡
ፓርቲው አፋጣኝ እርዳታ አስፈላጊ ቢሆንም የትግራይን ቀውስ ሙሉ በሙሉ መፍታት የሚችለው መዋቅራዊ ለውጥ ብቻ መሆኑን አፅንዖት ሰጥቷል፡፡
በትግራይ ክልል ህፃፅ የተፈጠረዉ ርሀብ የሁሉም መጠላያ ጣብያዎች ማሳያ መሆኑን መግለጫዎቹ ያሳያሉ።
ህወሃት ከተፈናቃዮች ላይ ጭምር የአባልነት መታወቂያ እየወሰደ ተፈናቃዮችን ለከፍተኛ ችግር መዳረጉን የሚደርሱበት ክሶች ያሳያሉ፡፡
አቶ ደጋፊ ሀደራ የትንሳኤ ስርዓት ቃንጪ ፖርቲ ሊቀመንበሮ ሲሆኑ ለዚህ ቀዉስ ዋናኛ ተጠያቂዉ ህወሃት ነዉ ይላሉ።
ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት ) በበኩሉ በተለያዩ መንገድ የሚቀርብበትን ክስ ዉድቅ የሚናደርግ ሲሆን የፌደራል መንግስቱን በፊናዉ ይወቅሳል፡፡
የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያዉን የሰላም ስምምነት ሙሉበሙሉ መተግበር ባለመቻሉ የትግራይ ህዝብ ለዘርፈ ብዙ ችግሮችን እንዲዳረግ አድርጓል በሚል የህፃፅን ርሀብ አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ ወቅሷል፡፡
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር በበከሉ በክልሉ ህፃፅ የተፈናቃዮች መጠለያ ያጋጠመዉን ርሀብ ለመደገፍ የተደረገዉን የህዝብ ርብርብ አመሰግኗል።
ነገር ግን ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ማኖርየሚቻለውተፈናቃዮች ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ቄያቸውመመለስና ማቋቋም ሲቻል መሆኑን አስረድቷል።
የፌደራል መንግስትም አሁንም ለዚህ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ተፈናቃዮችን ወደ ቦታቸው በተቻለ ፍጥነት እንዲመለሱ እንዲያደርግ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
የትንሳኤ ስርዓት ቃንጪ ፖርቱ ሊቀመንበር አቶ ደጋፊ ሀደራከህወሃት በተጨማሪ የፌደራል መንግስትም ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የፌደራል መንግስቱ ዜጎቹን የመጠበቅና ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው መመለስ ነበረበት ሲሉም ተናግረዋል።
በሌላ መልኩ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንም በትላትናዉ ዕለት ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ አዉጥቷል።
በመግለጫዉም መንግሥት በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት በማድረግ የምግብ ሰብዓዊ ድጋፍ እያቀረበ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
በህፃፅ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ዜጎችም ዓመቱን ሙሉድጋፍ ሲደረግላቸው መቆየቱን ነው ኮሚሽኑ ያስገነዘበው፡፡
ነገር ግንለተፈናቃይ ማህበረሰብ የሚላከው ድጋፍ ለታለመለት አላማ ብቻ መዋሉንየማረጋገጥና ክፍተቶች ቢኖሩም እንዲሟላ የማድረግ ሃላፊነት የክልሉና የአካባቢው ጊዜያዊ አስተዳደር መሆኑን ሊታወቅ ይገባል ሲልም ገልፃል፡፡
የህፃፅ ተፈናቃዮችን በተመለከተ መግለጫ ካወጡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ይገኛል፡፡
የድርጅቱ ምክትል ዳይሬክተር አቶ መብሪህ ብርሀኔ በበኩላቸው በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች በመሆናቸው ሁሉም ሀላፊነቱን መውሰድ አለበት ብለዋል፡፡
በዋናነት ደግሞ የሰላም ሚኒስቴር ሰላምን ተፈናቃዮችን ወደ ሀገር ለመመለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሊሰራ ይገባል ሲሉም ገልፀዋል፡፡
አቶ መብሪህ አክለውም ሀላፊነት መውሰድ ያለበት ሁሉም ሀላፊነረቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
በተለይም የግዚያዊ አስተዳደሩም ሆነ የፌደራል መንግስቱ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራውን ሊሰራ እንደሚጋበም አስድተዋል፡፡
ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ / ህወሃት / ተፈናቃዮችን ችግር ህዝብ እዳያውቅ ደብቋል ከሚል ክስ እስከ ተፈናቃዮች ገንዝብ መሰብስብ ወቀሳ ደርሶበታል፡፡
የሳልሳይ ወያነ ትግራይ /ሳወት / ኮምኒኬሽን ሀላፊ አቶ ብርሀነ አፅብሃ ድርጅቱ ተፈናቃየጶችን በግዴታ ገንዘብ እንዲሰጡ እያደረገ ነው ሲልም ወቅሷል፡፡
በተለይም አሁን ችግር በተከሰተበተ ሽረ ከተማ ከሚገኙ የተፈናቃይ ካምፕ ውስጥ መወጮ ያላዋጡ ዜጎችን መጠለያ አፍርሷ እስከማባረር መድረሱን ገልፃል፡፡
አሁን ተፈጠረው ችግር ከእርዳተው ጎን ለጎን ፖለቲካዊ መፍትሄ ዋናኛው መሆን አለበት የሚሉት አቶ ደጋፊ ሀደራ በዋናነትም ፕሪቶቶሪያው የሰላም ሰምምነት መከበር አለበት ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በክልሉ ሁሉን አካታች ሆነ የግዚያዊ አስተዳደር ማደረግ አለበት የሚሉት አተፖ ሀደራ አሁንበክልሉ ችግሮች የተባባሱት ክልሉ መሪ በማጣቱ ነው ብለዋል፡፡
ትግራይ ክልል የሚያስተዳደር አካል ያስፈልጋል ያሉም ሲሆን ትግራይ ክልል አሁን መንግስት የለውም ሲሉም ወቅሰዋል፡፡
ተፈናቃዮች ወደቀያቸው መመለስ ሁሉም ችግሮች መፍትሄ መሆኑ የሚገለፅ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ሙሉለሙሉ መተግበር አለበት ተብሏል፡፡
አሁን በትግራይ ህፃፅ መጠለያ ጣብያ የተከሰተው ችግር በሌሎችም ተፈናቃይ መጠለያዎች ውስጥ ሊከሰተ የሚችል በመሆኑ ግዚያዊ አስተዳደሩም ሆነ ፌደራል መንግስት ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባከል ሲሉም ያነጋገርናቸው ፖለቲከኞች እና ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አሳስበዋል፡፡
በህፃፅ የተፈጠረው ርሃብ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ እና እርዳተው ያለበት ሁኔታን በተመለከተ የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር አደጋ ስጋት እንዲሁም ጤና ቢሮን ለማካተት ያደረግነው ሙከራ ለግዜው ሊሳካልን አልቻለም፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ