ከህወሓት ተነጥለው የወጡ ከፍተኛ አመራሮች የመሰረቱት ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፖርቲ የመመስራቻ ጉባኤውን በአዲስ አበባ በማካሄዱ ይታወሳል።
በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ ለዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም መሰጠቱም የሚታወስ ነዉ።

አቶ ጌታቸው ፓርቲው በትግራይ ጉባኤውን ለማድረግ ፍላጎት የነበረው ቢሆንም በክልሉ ያለው ስርዓት አልበኝነት ጫፍ የደረሰ በመሆኑ ማካሄድ አለመቻሉን አስታዉቆ ነበር።
ፖርቲዉ በዛሬዉ ዕለት ደግሞ የድርጅቱን ምክርቤት (ማእከላይ ኮሚቴ) ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።
መግለጫዉን የሰጡት አቶ ጌታቸዉ ረዳ ይመሩት በነበረዉ ግዜያዉ አስተዳደር ከንቲባ ተደርገዉ ተሹመዉ በህወሓት ተቃዉሞ ስራቸዉን እንዳይሰሩ ታግደወ የቆዩትና ዲሞክራሲ ስምረት ትግራይ ፖርቲ መስራቾች አንዱ የሆኑት አቶ ብርሀነ ገብረየሱስ ናቸዉ።

አቶ ብርሀነ ገብረየሱስ የፖርቲዉ ስራ አስፈፃሚ አባልና የሚዲና ኮሚኒኬሽን ሓላፊም ናቸዉ።
ከወር በፊት ይፋዊ ጉባኤዉን ማድረጉን ያስታወሱት ሓላፊዉ የዛሬዉ ስብሰባ ሶስት ዋና ዋና ዓላማዎች እንዳሉት ገልፀዉ የትግራይ ህዝብ የነበረበትን የጭቆና ቀንበር ለመጣል ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
ያለፈዉ ጦርነት በርካታ ወጣቶችን ያጠፋ በመሆኑ ትግራይ አማራጭ ሰለማዊ ፖለቲካ ፖርቲ ስለሚያስፈልጋት የመጣ መሆኑንም ገልፀዋል።
ፓርቲውለትግራይ ህዝብ አማራጭ ለመሆን እንዲሁም በቀጣጠይ በትግራይም ሆነ በሀገሪቱ የሚደረገረውን ምርጫ ለመሳተፍ በማለም እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ "በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ዐዋጅ ቁጥር 1133/2011" እና "በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011" መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ ኃላፊነት እንደተሰጠው ይታወቃል፡፡

በዚህም መሠረት ምስረታውን ያደረገው ዲሞክራሲያዊ ስምረት ፓርቲ በትግራይ ክልል ይህ ነው የሚባል እንቅስቀሴ እያደረገ ባይሆንም በአዲስ አበባ ያሉ አመራሮቹ የማዐድላዊ ኮሚቴ ስብሰባቸው ጀምረዋል፡፡
የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባል እና የሚዲያና ኮምኒኬሽን ሐላፊ አቶ ብርሀነ ግበረየሱስ የዛሬው ምክር ቤት ሰውሎ ሶስት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመጀመሪያው በቀጣይ አንድ ዓመት ዕቅድ ማውጣት መሆኑን ተናገሩ ሲሆን በመቀጠል ዕቅዱን የሚያስፈፀሙ በየደረጃው አመራሮችን መምረጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪ ደግሞ ፓርቲው ሚመራበት የፖለቲካ ፍኖታ ካርታ ከክልሉ እና ከሀገራዊ አኳያ የሚታይበትበ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ፓርቲው በመቀሌ በከፈተው ዋና ቢሮው ላይ የታጠቁ አካላት በሐምሌ 2017 ዓ›ም ጥቃት እንደፈጸሙበት ከገለጠ በኋላ ፓርቲው በትግራይ መስራች ጉባኤውን ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ እንደሌለ በመግለጽ ለምርጫ ቦርድ ቅሬታ አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ስምረት ፓርቲ ይህንኑ መስራች ጉባኤውን ያካሄደው የጀመረው መስራች አባላቱን ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ በመጥራት መሆኑንም መግለፁ ይታወሳል፡፡
ሆኖም በትግራይ ክልል የሚገኙ ሁሉም የፓርቲው አባላት በዚህ መስራች ጉባኤ ላይ መሳተፍ አለመሳተፋቸውን ግን የተረጋገጠ መረጃም አልተገኘም፡፡
ፓርቲው ትግራይን ላይ ሆነ በሀገሩቱ የስልጣን ባለቤት ህዝብ በመሆኑ ምርጫው ላይ ተሳትፈን አማራጭ ሀሳብ ለመሆን በማለም ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በቀድሞውም በክልሉ እስቃሰሴ ማድረግ ያለተቻለው በክልሉ ያለው ስረዓት አልበኘነት ከፍተኛ በመሆኑ ነው ሲሉም የክልሉን ግዚያዊ አስተዳደር ወቅሰዋል፡፡
አብዛኞቹ የስምረት ፓርቲ ጥንስስ መስራቾች በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሕጋዊ የፖለቲካ ሰውነቱን ያጣው ሕወሓት የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ከፓርቲው መሥራቾች መካከል ቀደም ሲል የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዱሁም አሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑትን ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የተወሰኑት በአሁኑ ወቅት በፌደራሉ መንግሥት ሥልጣን ተሰጥቷቸው የሚገኙ አመራሮች ይገኛሉ፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2108 ዓ.ም እንደሚካሄድ መግለፁ የሚታወስ ነው፡፡
ይህንን ተከትሎም ስምረት ፓርቲ በምርጫው ለመወዳደረዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም በዛሬው ምክር መግለጫው ላይ ገልፃል፡፡
አሐዱም ለመሆኑ አሁን በትግራይ ክልል ያሉ አንገብጋቢ ችግሮች መፍትሄ ሳያገኙ ምርጫ ማድረግ ይቻላል ወይ ሰንል ጠይቀናል፡፡
አቶ ብርሀነ ይህንንም ሲመልሱ ምርጫ አማራጭ የሌለው ጉደይ ነው ያሉም ሲሆን ትግራይ የተመረጠ መንግስት ሊያስተዳድራት ይገባል ብለዋል፡፡
በክልሉ ያሉ ችግሮችን እንዲሁም ተፈናቃዮችን እንዲሁም ተያዙ መሬቶችን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሠረት መተግበር አለበት ብለዋል፡፡
ነገር ግን አሁን ትግራይ ላይ ይሉታ ያለው ያለውን ችግር የሚፈታ አካል ባለመኖሩ ክልሉ በህዝብ መረጠ መንንግስት ያስፈልገዋል ሲሉም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ግዜያዊ አስተዳደሩ ሁሉን ያቀፈ አንዲሆን ስለሚደነግግ በዚህ መሰረት ብዙዎች የክልሉ ፖለቲካ ይስተካከላል በሚል ተስፋ አድርግው ነበር።
ነገር ግን በፖለቲካ ምህዳሩ ምክንያት ተፈጻሚ አለመሆኑ የብዙዎችን ተስፋ ያደበዘዘ ባለበት ሁኔታ 7ኛዉ ብሔራዊ ምርጫ ግንቦት 24 እንደሚካሄድ ቦርዱ ከሰሞኑ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ በበኩሉ ህጋዊ ዕዉቅናዉ ካልተመለሰ በክልሉ ምርጫ ማድረግ አይታሰብም ያለ ሲሆን ይህንን በማስመልከት ሀሳብ የሰጡት በዚህ የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሐይሉ ቦርዱ ከህወሓት ጋር ምንም አይነት ንግግር አለማድረጉን ገልጸዋል።

ፓርቲው በትግራይ ከልል ምርጫ ለማድረግ ዝግጀቱን ማድረጉንም በዛሬው ዕከለት የገለፀ ሲሆን የፓርቲው ማዕጀላዊ ኮሚቴው የተለያዩ ውሳኔዎችን ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
አሐዱም ለስራ አስፈፃሚው አባልና ለሚዲያና ከምኒኬሽን ሐላፊው ለመሆኑ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የመጣመር ፍላጎት አላችሁ ወይ ሲል ጠይቋል፡፡
ይህ ጥምረት ከብልፅግና ፓርቲ ጋርም ቢሆን ልታደረጉት ትችላላችሁ ወይ ስንል ለጠይቅነው ጥያቄ ምላሽ ተሰጥቶል፡፡
አቶ ብርሀነ በምላሻቸው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ጥመረት ስለመፍጠር በሂደት ምናየው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
ከብልፅግና ፓርቲ ጋር የሚያያዙ ግን ሂነ ብለው ነው ያሉም ሲሆን ስምረት ከብልፅግና ጋር ቢሰራ ችግር የለውም ነገር ግን እንደ ህወሓት አመራሮች ከሌሎች ሀገራት ጋር ሆኖ ሀገርን ለማጥቃት ማሰብ ነው ሊኮነን የሚገባው ሲሉም ገልፀዋል፡፡
ስምረት ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ስምረት ፓርቲን ያቋቋሙት በደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመሩት የሕወሃት ቡድን በተራዘመ የአስተዳደር ግልበጣ ሴራ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳነት መንበራቸው እንዲለቁ ግፊት ስለተደረገባቸው መሆኑን መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
የትግራይ ፀጥታ ኃይል ስምረት ፓርቲ በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሰውን የትግራይ ታጣቂ ቡድን ይመራል በማለት ካሁን ቀደም መወንጀሉም አይዘነጋም፡፡
ስምረት በበኩሉ አመራር የሚሰጠው አንድም ታጣቂ ቡድን በስሩ እንደሌለ ገልፃ በወቅቱ ውንጀላውን አስተባብሏል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ