መስከረም 12/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የ2018 የትምህርት ዘመን መጀመሩ ተከትሎ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ከወራቶች እረፍት በኋላ ተመለሰው ትምህርታቸው እየተከታተሉ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ በሚሰጠው የመማር ማስተማር ሂደት ልዩ ፍላጎት የሚሹ ዜጎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በትምህርት ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

በየትኛውም ትምህርት ቤቶች ልዩ ፍላጎት የሚሹ ተማሪዎች የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ተካታችን እንዲሆኑ የሚያስችሉ አሰራሮች ስለመኖራቸው የትምህርት ባለሙያው ሳሙኤል አሰፋ (ዶ/ር) ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

እንደ ባለውያው ገለጻ ልዩ ፍላጎት የሚሹ ተማሪዎች እንደ ማንኛውም ተማሪ ትምህርታቸውን ምቹ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዲከታታሉ የተቀመጡ አሰራሮች ቢኖሩም፤ ተግባራዊ እንዲሆኑ ከማስቻል አኳያ ሊራበት ይገባል፡፡

ልዩ ፍላጎት የሚሹ ተማሪዎች ወደኋላ እንዳይቀሩ እና ትምህርታቸውን በመከታል ውጤትን እንዲቀዳጁ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና እንደሚጠይቅ ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ባለሙያው አቶ ዳምጣቸው መስፍን በበኩላቸው፤ ለተማሪዎች ምቹ የመማር ማስተማር ሂደት በመፍጠር እና በሰለጠነ መምህር ትምህርታቸውን እንዲከታቱ ማስቻል ተገቢነትን አንስተዋል፡፡

በሰለጠኑ እና አቅም ባላቸው ባለሙያዎች ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲከታታሉ ማስቻል ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ አስቻይ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ በተጨማሪም ተማሪዎች የራሳቸውን ጥረት በመጨመር በትጋት ትምሀርታቸውን ሊከታታሉ ይገባል ብለዋል፡፡

አክለውም ልዩ ፍላጎት የሚሹ ዜጎች በትምህርት ሥነ ምህዳሩ ላይ ተካታች እንዲሆኑ እና የትምሀርት አሰጣጡ ልዩ ፍላጎት የሚሹትን የዋጁ ሊሆን እንደሚገባ ለአሐዱ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም የ2018 የትምርት ዘመን መጀመሩን ተከትሎ፤ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉት ሁሉ ልዩ ፍላጎት የሚሹ ተማሪዎች ወደኋላ እንዳይቀሩ ትኩረት ሊሰጣቸውን ይገባል ሲሉ የትምህርት ባለሙያዎቹ አሳስበዋል፡፡

ልዩ ፍላጎት የሚሹ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመከታል የተሻለ ውጤትን እንዲያመጡ አስቻይ ሁኔታን መፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት በመሆኑ፤ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ