ጥቅምት 1/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ቴክኖ ኢትዮጵያ አዲሱን የስልክ ሞዴል ማስተዋወቂያ እና በካሞን 40 በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተነሱ ፎቶዎች ኤግዚቢሽን መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር አካሂዷል፡፡
በዚሁ ዝግጅት ከ'ቦርድ ሴል ፎን' አዲስ አበባ ጋር በመተባበር በሀረር፣ ድሬዳዋ፣ ቁንዱዶ ተራራ እና አዲስ አበባ የተነሱ 250 ፎቶዎች ለዕይታን በኤግዚቢሽን መልክ የቀረቡ ሲሆን፤ ፕሮግራሙ የተለያዩ ሽልማቶችን የሚያሸልሙ አጓጊ ጨዋታዎችና የሙዚቃ ዝግጅቶችም ቀርበዋል፡፡

በመርሓ ግብሩ ከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊዎች፣ የፎቶ ባለሙያዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ የቴክኖሎጂ አድናቂዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
በተጨማሪም ሙሉ ቀን በዋለው በዚህ ፕሮግራም ላይ ከ40 ሺህ በላይ ተመልካች ተገኝተው ፎቶዎችን በመጎብኘት በዝግጅቱ መታደም ችለዋል፡፡
ከዚህ በፊት በካሞን 30 የስልክ ሞዴሉ የተነሳ የፎቶ ኤግዚቢሽን ያካሄደው ቴክኖ ኢትዮጵያ አሁን ደግሞ በካሜራ እና በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ከፍ ብሎ በመጣው የቴከኖ ካሞን 40 የስልክ ሞዴሉ የኢትዮጵን ባህል፣ ቀለምና፣ መልከኣ ምድር የሚያሳዩ ፎቶዎችን ለሁለተኛ ጊዜ ለዕይታ አቅርቧል፡፡

በዝግጅቱ አዲሱ የቴክኖ ታበሌት ሜጋ ፓድ፣ የተለያዩ የቴክኖ ሞዴል ስልኮች፣ ኤር ፖዶች፣ ስማርት ሰዓቶች፣ ላፕቶፖች እና ሌሎችም የኩባንያው ምርቶች ለጎብኚዎች ተዋውቀዋል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ