ሕዳር 25/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦን ላይን በማስተዋወቅ ያለ ደረሰኝ የሚደረጉ ግብይቶችን ለማስቀረት አዲስ አሰራር እየተዘረጋ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ያለ ደረሰኝ በኦን ላይን የሚደረጉ ግብይቶች ሕጋዊ ባለመሆናቸው ቁጥጥርና ክትትል የሚያደርግ አዲስ ክፍል (ዲፓርትመንት) መቋቋሙን ለአሐዱ ሬዲዮ ገልጿል።

የኦን ላይን ግብይትን የሚደግፍ መሆኑን የገለጸው ንግድ ቢሮው፤ ነገር ግን ያለ ደረሰኝ ማንኛውን ነጋዴ መሸጥ እንደማይገባው አሳስበዋል።

Post image

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በኦን ላይን የሚደረጉ ግብይቶችን በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥጥር እና ክትትል ለማድረግ በቢሮው አዲስ ዲፓርትመንት ተቋቁሞ ወደ ሥራ በመግባት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም ሁሉም ማህበረሰብ እየተደረገ ያለውን ቁጥጥር ሊገነዘበው ይገባል ሲሉ ኃላፊው ገልጸዋል።

ማንኛውም ነጋዴ በኦን ላይን ግብይት ሲፈጽም በደረሰኝ ሊሆን እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን፤ ምርቶቻቸውን ከቦታ ቦታ በማድረስ የሚሸጡ ቢኖሩም ደረሰኛቸውን ይዘው መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው አስምረውበታል።

ይህንን መመሪያ በሚተላለፉ ነጋዴዎች ላይም ከፍተኛ የሆነ የቁጥጥር እና ክትትል በማድረግ እርምጃ እንደሚወሰድ አጽንኦት ሰጥተውበታል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ