ጥቅምት 10/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጂድ የዱዓ እና የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ለ40 ዓመታት ባስተማሩበት ኑር መስጂድ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶበታል።
በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይም ኡለማዎች፣ ደረሳዎች፣ ኡስታዞች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት አስክሬናቸው ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተሸኘ ሲሆን፤ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የክብር ሽኝት ከተረገላቸው በኋላ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈፀም ይሆናል።
ፎቶ፦ ኢዜአ እና ኢቢሲ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ