ሰኔ 24/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የአገልግሎት ፍቃዱን ከተረከበ በአራት ዓመታት ውስጥ፤ በሀገሪቱ ዙሪያ ያሉ የ90 ቀናት ንቁ ደንበኞቹ ቁጥር 10 ሚሊዮን መድረሱን ገልጿል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄለፑት እንደተናገሩት፤ የቴሌኮም ኩባያው በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አራት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ በእነዚህ አራት ዓመታት ውስጥ 300 ቢሊየን ብር በላይ ሙዓለ ንዋይ ወጪ አድርጓል፡፡

Post image

የ90 ቀናት ንቁ ደንበኞቻችን ቁጥር 10 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ 7 ነጥብ 1 ሚሊዮን የሞባይል ዳታ አገልግሎት ተጠቃሚዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

አክለውም አሁን ላይ ኩባንያው 900 ሠራተኞች ሲኖሩት ከእነዚህ ውስጥ 97 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን በመግለጽ፤ በተጨማሪም ከ20 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ተዘዋዋሪ የሥራ ዕድል መፍጠሩ ገልጸዋል።

ሳፊሪኮም ኢትዮጵያ በየቀኑ 31 ሺሕ አዳዲስ የአገልግሎት ተጠቃሚዎች ደንበኞችን እየተቀላቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Post image

በአሁኑ ሰዓት ካሉት ደንበኞች 75 በመቶዎቹ በቋሚነት አገልግሎቱን እየተጠቀሙ መሆኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጨምረው ተናግረዋል፡፡

አክለውም "በዚህ አራት ዓመት ውሰጥ ችግር ሆኖብን ነበረው፤ ተፎካካሪያችን በመንግሥት ባለቤትነት ያለ መሆኑ ነው" ብለዋል።

ሳፊሪኮም ኢትዮጵያ 3 ሚሊዮን ዶላር ለኢትዮ ቴሌኮም ለመሠረተ ልማት ኪራይ እንደሚከፈል የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ ኩባንያው የሚጠበቅነትን ግብር እስካሁኑ ሰዓት ድረስ በቴሌብር እንሚከፍል ተናግረዋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ