መስከረም 27/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ትምህርት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (ሪሜዲያል) ፕሮግራም መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሠረት፡-
👉 የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216

👉 የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204

👉 ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

👉 የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማትለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

👉 ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165 መሆኑን አስታውቋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49 ነጠብ 5 በመቶ በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የሪሜዲያል (Remedial) ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጿል።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33 በመቶ ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግሥት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የሪሜዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ