ጥቅምት 19/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የትምህርት ተቋም ምደባ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሠረት ተማሪዎች የተቋም ምደባቸውን ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የሚችሉ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ መሠረት፤ የ Remedial ፕሮግራሙን እንዲከታተሉም ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

የተማሪዎች የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት 👇
በድረ-ገፅ፦ https://student.ethernet.edu.et
በቴሌግራም ቦት፦ @moestudentbot

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ