መስከረም 16/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተገኝተው የመስቀል ደመራ በዓልን በጸሎት አስጀምረዋል።

Post image

በበዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሐዲያ እና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎች እና ምእመናን ተገኝተዋል፡፡

እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ምእመናን እና ቱሪስቶች በዓሉን እያከበሩ ይገኛል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ