ጥቅምት 12/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የትምህርት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ እና የመማር ማስተማሩን ሂደት በተገቢው መንገድ ለማስኬድ የተለያዩ ሕጎችና መመሪያዎች ያሉ ሲሆን፤ የመምህራን የሙያ ሥነ-ምግባር ደንብ አንዱ ነው።

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር)፤ የመምህራን ሙያ ሥነ-ምግባር ደንብ የማውጣት ስልጣን አዋጅ በተሻሻለው የትምህርት አዋጅ መሠረት የመምህራን ማህበር መሆኑን መረጋገጡን ገልጸዋል።

ስለሆነም ደንቡ መምህራን ሙያቸውን አክብረው ኃላፊነታቸው እንዲወጡ በሚያስችል መልኩ ለመከለስ መወሰኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 23ኛ መደበኛ ጉባኤ ''ለትምህርት ስርዓታችን ተጠያቂነት የድርሻችንን እንወጣለን'' በሚል ባካሄደው ጉባኤ የተደረጉ ማሻሻያዎች ላይ አስተያየቶችና ምልከታ በማድረግ ጉባኤው አጽድቆታል ብለዋል።

"ደንቡ ላይ የተደረገገው ማሻሻያ አስፈላጊ ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የሥነ-ምግባር ችግር ያለባቸውን መምህራን ለማረም የሚያግዝ ነው ብለዋል።

ይህን የሙያ ሥነ-ምግባር ደንብ መተላለፍ እንደ አንድ ዲሲፕሊን ጥሰት የሚታይ ነው ሲሉም ጠቁመዋል።

ደንቡ በደርግ ዘመነ መንግሥት ለመጀመሪያ ጊዜ መውጣቱን አስታውሰው፤ ከጊዜ ሁኔታ ጋር እየተሻሻለ የመጣበት አግብባ መኖሩን ገልጸዋል።

ይህም መመሪያ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች መብት እና የሚከተሏቸው ሙያዊ ሥነ-ምግባሮችን የያዘ እንደሆነ ተመላክቷል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ