መስከረም 20/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2018 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከመስከረም 20 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በዚህም መሠረት አመልካቾች የመመዝገቢያ ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ እንደሚችሉ የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ ገልጿል።
አመልካቾች ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው ጥያቄ ዘወትር በሥራ ሰዓት በ0920157474 ወይም 0911335683 እንዲሁም በኢሜይል አድራሻ ngat@ethernet.edu.et በኩል ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ሁሉም አመልካቾች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሊኖራቸው እንደሚገባም ማሳሰቢያ ተላልፏል።
በተጨማሪም አመልካቾች የምዝገባ እና የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በቴሌብር (TeleBirr) በኩል ብቻ መከፈል እንደሚኖርባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
የ2018 የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና ምዝገባ ከመስከረም 20 እሰከ 25 እንደሚካሄድ ተገለጸ
