መስከረም 21/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ትምህርት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤትን ከ300 ወደ 297 ዝቅ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተማሪዎች ወደቀጣይ የትምህርት ደረጃ ለመዛወር 50 በመቶና ከዚያ በላይ ማምጣት እንዳለባቸው እንደሚደነግግ ይታወቃል።
በዚህ መሠረትም በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና አማካይ ውጤታቸው 49 ነጥብ 50 እስከ 49 ነጥብ 99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ወደ 50 በመቶ እንዲጠጋጋ መወሰኑን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን መስከረም 20/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ደብዳቤ አመላክቷል፡፡

ይህንንም ውሳኔ ተከትሎ 49 ነጥብ 5 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ እንዳሟሉ ተደርጎ እንደሚወሰድ ተገልጿል፡፡
በመሆኑም 49 ነጥብ 5 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ