መስከረም 21/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በግንባታ ላይ የነበረ ቤተክርስቲያን መሸጋገሪያ እንጨት ተደርምሶ የ36 ምዕመናን ሕይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡
በወረዳው በአረርቲ ከተማ አስተዳደር አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ክብረበዓልን አስመልክቶ ዛሬ መስከረም 21/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:45 ላይ በግንባታ ላይ ያለ ቤተክርስቲያን እየተጎበኘ ባለበት ሰዓት አደጋው መድረሱ ተገልጿል፡፡

በዚህ ጉብኝት ወቅት ለፊኒሺንግ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ 36 ምእመናን ሞት እንዲሁም በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የወረዳው ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
እስካሁን ድረስ በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች እና በአደጋው በደረሰው ጉዳት ከ200 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸቀው በአረርቲ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ መሆኑ ተነግሯል።