መስከረም 12/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች እስከ መስከረም 14 ድረስ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን ማስተካከል እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት አምጥተው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከተጠቀሰው ቀን ድረስ ማስተካከል የሚችሉ መሆኑን ነው የገለጸው።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን እንደሚቀበል የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ ተማሪዎች ምርጫቸው ውስጥ ማካተት የሚችሉ መሆኑን አስታውቋል።

እንዲሁም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምርጫ ውስጥ የማይካተቱ መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ