ሕዳር 6/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ“ውድብ ወለዶ ትግራይ (ወለዶ)" ሕጋዊ የክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት መስጠቱን አስታውቋል።
ቦርዱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ በዐዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለ“ውድብ ወለዶ ትግራይ (ወለዶ)" ሕዳር 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሕጋዊ የክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት መስጠቱን አስታውቋል።

የትግራይ ትውልድ ፓርቲ ወይም 'ውድብ ወለዶ ትግራይ' የተሰኘው ይህ አዲስ ፓርቲ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የቀድሞ የህወሓት አባላት የመሰረቱት ፓርቲ ሲሆን፤ በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ በመቐለ ከተማ ጠቅላይ ጉባኤውን ማካሄዱ ይታወሳል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ