ሕዳር 16/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስደተኞች እና ተመላሽ አገልግሎት ጋር በተያያዙ የ2018 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል።

የኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመለሾች አገልግሎት ኃላፊ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን የአገልግሉቱን የ2018 በጀት አመት የሶስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለቋሚ ኮሚቴው አቅርበዋል።

Post image

በዚህም እንደ ሀገር ስደተኞችን የማብዛት ፍላጎት አለመኖሩን የገለጹት ዳይሬክተሯ በሀገር ውስጥ የድንበርም ሆነ የአየር መንገድ የሚመጡ ዜጎችን ሁሉ እንደስደተኛ መቀበል እንደማይቻል ገልጸዋል።

መቀበል የማይቻልበት ምክንያትን ሲያብራሩም፤ "በኢትዮጵያ ያሉ ዜጎችን ሁሉ እንደ ስደተኛ ከተቀበልን ከመሰረቱ ላይ ያሉ ችግሮች ሰፊ በመሆናቸው በርካታ ዜጋ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ይችላል" ሲሉ አንስተዋል።

ይህም ለሀገር ደህንነትና ጸጥታ ስጋት የሚሆን ነው ያሉት ዳይሬክተሯ፤ "እንደ ሀገር ወይን ተቋም ስደተኛን የማሳደግ ፍላጎት የለንም" ብለዋል።

አሁንም በሀገር ውስጥ ያለው የስደተኛ ቁጥር ካለው ሕዝብ 1 ነጥብ 1 በመቶ የሚይዝ መሆኑንና የስደተኞች ጉዳይ በአይነቱ ልዩ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሌሎች ሀገራት የፓሊሲ ለውጦችን ማድረጋቸውና በራቸውን መዝጋታቸውን የገለጹት ዳይሬክተሯ፤ በተለይም ባደጉ ሀገራት ሲተገበር በግልጽ እየታየ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በበኩሏ አሁን ክልከላ አለማድረጓና ስደተኞችን እየተቀበለች ባለው አቅምና ሀብት መጠን ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዳይሬክተሯ ሪፓርት ባሻገር በጋምቤላና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሌሎች አካባቢዎች ለሀገር ስጋት የሚሆኑ ድርጊቶች መኖራቸው ከምክር ቤት አባላት ተነስተዋል። ስለሆነም እነዚህን ስጋቶች መቀነስ እንደሚገባም ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ ከሚገኙ ስደተኞች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች ሲሆኑ፤ 33 በመቶ የሚሆኑት የሶማሊያ፣ 17 በመቶ የኤርትራ ስደተኞች መሆናቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ