በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን ገምግሟል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ዩኒቨርሲቲውን የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት መሰረት በማድረግም የቴክኖሎጂ ምርምርና የዕውቀት ሽግግር ላይ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በቋሚ ኮሚቴው አባል ወይዘሮ ሱመያ ደሳለው ዩኒቨርስቲው የክዋኔ ኦዲት ግኝት በተመለከተ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፤ ዩኒቨርሰቲው በርካታ የኦዲት ግኝቶች እንደተገኙበት አብራርተዋል፡፡

Post image

ዩኒቨርሰቲው መመሪያ በማውጣትና የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ግኝቶችን ለማስተካከል የተሰሩ ሥራዎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ ቀሪ በሂደት ላይ ያሉ ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ ማከናወን እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል የተቋረጡ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን ከሀገራዊ ተልዕኮው አንፃር ዓላማቸውን እንዲያሳኩ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

ለአንድ ተመራማሪ ከአንድ መቶ ሺሕ ብር በላይ መክፈል እንደማይቻል ዩኒቨርሰቲው ራሱ መመሪያ ያወጣ መሆኑን ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ ገልጸዋል፡፡

Post image


ይሁን እንጂ ዩኒቨርሰቲው ራሱ ላወጣው መመሪያ ጭምር ተገዢ አለመሆኑንም በግበረ መልሱ ወቅት የገለጹ ሲሆን፤ ከአቅም በላይ ሲያጋጥም ምን መደረግ አለበት የሚለውን በመመሪያው ላይ ማካተት ያስፈጋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በተጨማረም ዩኒቨርሰቲው ከምርምር ጋር በተያያዘ የሚያወጣቸው ወጪዎችን በሚመለከትም የኦዲት ምርመራ መደረጉን ዋና ኦዲተሯ ወይዘሮ መሠረት አብራርተዋል፡፡

በዚህ መሠረትም ከሚመከፈለው የምርምር ገንዘብ የምርመራ ሥራው ሳይጠናቀቅ ኦዲት ሥራው እስተከተናወነበት ወቅት ድረስ ለ24 የምርምር ሥራዎች ከ500 ሺሕ ብር በላይ ተለፍሎ መገኙቱን ዋና ኦዲተሯ ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርሰቲው በዚህ ጉዳይ ላይ ግምገማ እንደሚያደርግ መግለጹን ያኑሰት ዋና አዲተር መሠረት፤ "ክፍያ ሲፈፀም አፈፃፀሙ ቢገመገም ይህን ያህል ገንዘብ አይወጣም ነበር" ሲሉ ምላሹ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው ያልተጠናቀቁ የምርምር SEራዎችን በማጠናቀቅ የቴክኖሎጂ ምርምርና የዕውቀት ሽግግር ተደራሽነቱ ላይ ውጤታማ የሆነ ሥራ እንዲሰራም ተጠይቋል፡፡

የክዋኔ ኦዲት ግኝት እርምት ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ማስተካከል እንዳለበት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም ከፕሮጀክተፖች ጋር በተያያዘ ሁለት ፕሮጀክቶች በተያዘው ወቅት አለመጠናቀቃቸው ገልጸዋል፡፡

ካለመጠናቀቃቸው በተጨማሪም ፕሮጀክቶቹ ሳይጠናቀቁ ክፍያ መፈፀሙንም፤ በኦዲት ግኝት ወቅት እንደተደረሰበት ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ ተናግረዋል፡፡

ክፍተቶችን ለመሙላትም ዩኒቨርስቲው በቴክኖሎጂ የታገዘ የዕውቀት ሽግግር ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን እንደሚጠበቅበትም የቋሚ ኮሚቴው አባላት አስገንዝበዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በቀረበው የኦዲት ግኝት ላይ ጥያቄዎች ያነሱ ሲሆን፤ በዋናነትም ከምርምር ፈንድ ጋር በተያያዘ የተነሳ ይገኝበታል፡፡

Post image

በውጭ እርዳታ ለሚሰሩ ምርምሮች የሚሆን መመሪያ አለመዘጋጀቱ እንደክፍተት የታየ መሆኑን በማንሳት፤ ይህንን ሀብት እንዳይባክን የሚያሰጋ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሌላው "በናሙና ከታዩት 15 ፕሮጀክቶች መካካል ለሁለት ፕሮጀክት የአፈፃፀም ሪፖርት ሳይቀርብ ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሀምሳ ሺሕ ብር መለቀቁ ታይቷል" ያሉ ሲሆን፤ ለዚህ የተወሰደ ማስተካከያ እርምጃ መኖሩን ጠይቀዋል፡፡

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር)፤ በመመሪያ ክፍተት ምክንያት ያጋጠሙ ክፍተቶችን ለመሙላት በረካታ መመሪያዎችን አዘጋጅቶ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸዋል፡፡

Post image

ፕሬዝዳንቱ አብዛኞቹ ግኝቶች እየተሻሻሉ እንዳሉና ቀሪዎቹ ደግሞ በሂደት ላይ ያሉ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

በሪፖርቱ መሠረትም ከውጭ የሚገኝ ገንዘብ ላይ ያለው ሁኔታ እየበዛ በመምጣቱ መመሪያ ማስፈለጉን ያኑሱ ሲሆን፤ መመሪያው ተዘጋጅቶ በዩኒቨርሰቲው ሴኔት ቀርቦ መፀደቁን ተናግረዋል፡፡

ዩኑቨርሲቲውም በውጭ የሚያገኘው እርዳታ መመሪያ አውጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፤ ቀድሞ ኮሚቴው ቀርቦበት የነበረው ጥያቄም መስተካከሉን አንስተዋል፡፡

ሌላው ዩኒቨርሰቲው ከዚህ ቀደም ከምርምር ጋር በተያያዘ ክፍተት እንዳለበት ተደጋጋሚ ጊዜ ሲነሳበት እንደነበር ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል፡፡

ይህንንም መሠረት በማድረግ ማስተካካያ ማደረጋቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ማንኛውም የገንዘብ አወጣጥ ሪፖርት ሳይደረግ እንደማይወጣም ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ዶክተር ለሚ በተጨማሪም ዩኒቨርሰቲው ምርምርን በተመለከተ ለተመራማሪዎች ከመቶ ሺሕ ብር በላይ መክፈል እንደሌለባቸው መደንገጉን አንስተዋል፡፡

"ይህ መመሪያ ለምን አልተተገበረም?" በሚለው ሀሳብ ላይ ምላሽ የሰጡት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህንን በማስመለክት በፅሁፍ ተጠይቆ በዩኒቨርሰቲው በውይይት የተወሰነ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

Post image

በቋሚ ኮሚቴው አባል ወይዘሮ ሱመያ ደሳለው ማጠቃላይ ማብራሪያ የሰጡም ሲሆን፤ ዩኒቨርሰቲው ባለፈው ዓመት የተሰጡትን የኦዲት ግኝቶች ለማስተካከል የሄደበት ርቀት የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዋናነትም መመሪያ የሌላቸውን አሰራሮች መመሪያ በማወጣት እንዲሁም የቀሩ ፕሮጀክቶችን ከመፈፀም አኳያ ያለው ጅምር በጥሩ የሚታይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ዩኒቨርሰቲው ከኦዲቱ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የትምህርት ሚኒስቴር እና የገንዘብ ሚኒሰቴር ጉዳይ ጭምር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ዋና ኦዲተር አሰራሩን ተከትሎ ብቻ የሚሰራ መሆኑን መገንዘብ እንደሚያስፈልግም ወይዘሮ ሱመያ አሳስበዋል፡፡

"የሚሰሩ ምርምሮች ለማህበረሰቡ ምን ያህል የሚጠቅሙ እና ህዝብን የሚረዱ ናቸው? ወይስ የመደርደሪያ ማሟቂያ ሆነዋል? የሚለው መፈተሸ አለበት" ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ከግዢ ስርዓት ጋር በተያያዘ ከምዝገባ እስከ ግዢ ስርዓት በርካታ ችግር ስላለ የግዢ አዋጅ ማውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው የወጣውን አዋጅ እየተጠቀመበት ባለመሆኑ ይህንንም በማስተካከያነት ሊወስደው እንደሚገባው ወይዘሮ ሱመያ ተናግረዋል፡፡

የግዥ ስርዓቱን ማዘመን፣ የምርመር ሥራዎችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ከማድረግና ከፕሮጀክቶች አፈፃፀም አኳያ ያጋጠሙ ችግሮችን የክፍያ አፈፃፀምና የአዋጭነት ጥናትን አስመልክቶ ከመመሪያና ከአፈፃፀም ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ዩኒቨርስቲው የማሻሻያ ሪፖርት እስከ ጥር 15 ድረስ እንዲያቀርብ ቋሚ ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በዋናነትም መመሪያ የሌላቸው እና ምርምር እና የዕውቀት ሽግግሮችን በተመለከተ በሁለት ወራት ውስጥ ሪፖርት እንዲያቀርቡም ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ