ጥቅምት 10/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ በክቡር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን የኀዘን መግለጫ አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም "እግዚአብሔር በየዘመናቱ አገርን ያለ መካሪ፣ ሕዝብን ያለዘካሪ አይተወውም!" ብለዋል።

Post image

"ለዚህም ምስክሩ ታላቅ አረጋዊ፣ የበሳል አእምሮ ባለቤት፣ አገርን የሚወዱ፣ ሕዝባቸውን የሚያከብሩ፣ የተጠቁት ወዳጅ፣ የትውልድ አባት የሆኑት የክቡር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ነበሩ" ሲሉ ገልጸዋል።

"ኢትዮጵያ በጣት ከሚቆጠሩ አረጋውያን፣ አፈ ማር ከሆኑ መካሪዎችዋ መካከል አንዱ የሆኑትን፣ ለመወደድ የታደሉትን የዘመናችን ጌጥ ዛሬ አጥታለች" ያሉት ፓትሪያርኩ፤ "ይህንን የድካም ዓለም መገላገል ለእርሳቸው ዕረፍት ቢሆንም ለአገር ግን ታላቅ ጉዳት ከመሆኑም በላይ ዕድሜን ከጥበብ ጋር ያዋሐዱ በሁሉ ዘመን አይገኙምና ኀዘናችን ጥልቅ ነው" ብለዋል።

Post image

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

‎#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ