ጥቅምት 20/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) አዳዲስ የሚመሰረቱ ከተሞች የከተማ ስታንዳርድን ወይም ደረጃን በጠበቀ ፕላንና ዲዛይን መሠረት እንዲገነቡ እየተደረገ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።
አጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ 2 ሺሕ 543 ከተሞች መኖራቸውን የገለጹት፤ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ፈንታ ደጀን ናቸው።
ከእነዚህም ውስጥ የከተማን ደረጃ የሚያሟሉት 275 ብቻ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ከ2 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ደግሞ የማዘጋጃ ቤት ደረጃ ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህ ውጪ አዲስ አበባን ጨምሮ የክልል ዋና ዋና ከተሞች ላይ ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ ደረጃን ጭምር እንዲያሟሉ በማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የተሰሩ ከተሞችን ከማሻሻልና ከማደስ ባሻገር አዳዲስ ከተሞች ገና ሲቆረቆሩ የከተማ ስታንዳርድን ወይም ደረጃን በጠበቀ ፕላንና ዲዛይን መሰረት እንዲሰሩ የማድረግ ሥራ መጀመሩን ሚንስትር ዴኤታው አስታውቀዋል።
አዳዲስ የሚመሰረቱ ከተሞች ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ ፕላንና ዲዛይን እንዲገነቡ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሠረት የመኖሪያ ቤት አካባቢን፣ የአስተዳደር፣ የገበያ፣ የመናኸሪያ እና የመዝናኛ ቦታ የሚሉትን እንዲሁም አጠቃላይ ደረጃውን የጠበቀ የከተማ ፕላን እንዲኖረው አስቀድሞ ልየታ እንደሚደረግ አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ ከተሞች ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆን ለማስቻል የመሰረተ ልማት እና ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን የማሟላት ሥራም በስፋት እንደሚሰራበት አመላክተዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
አዳዲስ የሚመሰረቱ ከተሞች ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ ፕላንና ዲዛይን እንዲገነቡ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
 
  
  
  
 