ሕዳር 4/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 22ተኛ ኤርባስ ኤ350-900 አውሮፕላኑን በዛሬው ዕለት መቀበሉን አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ ዛሬ የተረከበው ይህ ዘመናዊ አውሮፕላን 21ደኛ ኤ350-900 አውሮፕላኑን ከተቀበለ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ኤር ባስ ኩባንያ የተረከበው ነው፡፡
ይህም በዓለም ዙሪያ ለሚያጓጉዛቸው መንገደኞቹ እጅግ ዘመናዊ፣ የላቀ እና ምቹ አገልግሎትን ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ስለመሆኑ አየር መንገዱ ገልጿል።
የኤር ባስ ኤ350-900 ሞዴል አውሮፕላን በመደበኛ ባለሦስት ክፍል አቀማመጥ ከ332 እስከ 352 መንገደኞችን የሚያስተናግድ ሲሆን፤ 18 ሺሕ ኪሎ ሜትር በረራዎችን ሳያርፍ መብረር የሚችል እንዲሁም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን እና የኤሮዳይናሚክስን ውጤቶችን ያካተተ ግዙፍ አይሮፕላን ነው፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
አየር መንገዱ 22ተኛ ኤርባስ ኤ350-900 አውሮፕላኑን ተቀበለ