ጥቅምት 4/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) በጂቡቲ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን በመቀበል ቃለ መኃላ ፈጽመዋል።

አምባሳደሩ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የሹመት ደብዳቤያቸውን በመቀበል የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ፊት ቀርበው ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።

Post image

ፕሬዚዳንት ታየ ለተሿሚ አምባሳደሩ የኢትዮጵያ እና የጂቡቲን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችል የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ታድመዋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ