ጥቅምት 27/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የቬንዙዌላውን ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን ከስልጣን ለማውረድ ወይም ለመግደል እቅዶችን ነድፏል ተባለ።

በቅርቡ የአሜሪካ ጦር በካሪቢያን ቀጠና መሽጎ የሚገኝ ሲሆን፤ ዋናኛ አላማውም የቬንዙዌላን ፕሬዝዳንት ለመግደል መሆኑን የሚያመለክቱ መረጃዎች ወጥተዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ ማዱሮንን በሕይወት ለመያዝ ከዛ ካለፈመ ባሉበት እንዲገደሉ እቅድ ያቀዱትበት ምክንያትም፤ "አደንዛዥ እጾችን ወደ አሜሪካ ከሚያስገቡ አማፂያን ቡድን ጋር ቁርኝት ፈጥረዋል" በሚል ክስ ነው።

በዚህም ትራምፕ አቅደውታል ተብሎ ሾልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ፤ ማዱሮን በሚደግፉ ወታደራዊ ተቋማት ላይ የአየር ድብደባ መፈፀም እንዲሁም የቬንዙዌላ የነዳጅ ማውጫ ቦታዎችን እና መሠረተ ልማቶችን መቆጣጠር መሆኑን አርቲ ኒውስ እና ዘ ኒዎዮርክ ታይምስ ዘግበዋል።

በሌላ በኩል የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ማዱሮን የት ተደብቀው እንደሆነ ባይታወቅም፤ ሀገራቸው "ለአሜሪካ የማትበረከክ ናት" ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም "የትራምፕ አስተዳደር የዓለም አቀፍ የእኩልነት ስርዓትን የማይቀበል ነው" ሲሉ ወንጅለው፤ ይህንን ደግሞ ቬንዙዌላ አትቀበልም ብለዋል።

"ሆኖም አጋር እንፈልጋለን" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በተለይ ሩሲያ፣ ቻይና ኢራን የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዲያደርጉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ባለፈው ወር ትራምፕ በቬንዙዌላ በመንግሥት ይደገፋሉ በተባለው ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ምክንያት የሲአይኤ ሥራዎች እንዲሰሩ ፍቃድ የሰጡ ሲሆን፤ ዋሽንግተን የባህር ሃይሎችን ወደ ምዕራባዊ ካሪቢያን ግዛት በማዘዋወር አደንዛዥ እጽ በሚያንቀሳቅሱ መርከቦች ላይ ከፍተኛ የአይር ጥቃት እንዲፈፀም ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ