ጥቅምት 11/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) በድሬዳዋ ደወሌ ባቡር ላይ በደረሰ አደጋ 14 ሰዎች ሲሞቱ 29 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

ከደወሌ መነሻውን አድርጎ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ባቡር ትላንት ሌሊት 8:00 አካባቢ በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ወረዳ ላይ በደረሰበት አደጋ 14 ሰዎች ሲሞቱ 29 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ከሽኒሌ ወረዳ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Post image

በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሽኒሌ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ ሲሆን፤ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

‎#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ