ሐምሌ 2/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዘንድሮው በጀት ዓመት 241 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 233 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 96.5 % ማሳካት መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
"ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት 83 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ወይም 45 በመቶ እድገት በከተማዋ ገቢ ላይ እድገት ያሳየ ነው" ያሉት ከንቲባዋ፤ ያልተሰበሰበው 8 ቢሊዮን ብር ከእርዳታ እና ብድር ይገኛል ተብሎ በተጨማሪ በጀት የታወጀ እንደነበር ገልጸዋል።
"ለውጥና እድገት በራስ አቅም ሲሆን መሰረቱ ሰፊ፤ ምሰሶውም ጠንካራ ይሆናል" ሲሉም ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባለሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
አክለውም ለተገኘው ስኬት የከተማዋ ነዋሪዎችን፣ ግብር ከፋዮችን፣ የገቢዎች ቢሮ ሠራተኞችና አመራሮችን እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
"በዘንድሮው በጀት ዓመት ከከተማዋ 233 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል" ከንቲባ አዳነች አቤቤ
