ሰኔ 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ‎እንደ አውሮፓ አቆጣጠ 2022 የዓለም ጤና ድርጅት ባጠናው ጥናት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሱስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ292 ሚሊዮን መብለጡ ተገልጿል።
‌‎
‎የጤና ሚኒስቴር የዓለም ፀረ-ሱስ ቀንን ምክንያት በማድረግ ‎"የቅድመ መከላከል፤ የማከም እና የተሃድሶ አገልግሎት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል፤ ለሚዲያ ባለሙያዎችና ለጤና ባለሞያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በቢሾፍቱ ከተማ ተሰጥቷል።

‎በዚህም በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዓለም አቀፍ ደረጃ 65 ነጥብ 5 የሚሆኑት የሱስ ተጠቂ የሆኑት ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል።

‎የጤና ሚኒስትር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሻሻል ሱሰኝነትን ጨምሮ በተለይም ተላላፊ፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን እና የአእምሮ ጤና ችግር ለመከላከልና ለመቆጣጠር ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

‎በዚህም የዓለም የፀረ-ሱስ ቀንን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ከሰኔ 18 እስከ ዛሬ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች የተከበረ ሲሆን፤ እንደ ሀገር እየጨመረ የመጣው ሱሰኝነት አሳሳቢ እየሆነ ነው ተብሏል።

‎በተለይ አምራች ሀይል የሚባለው ወጣቱ የማህበረሰብ ክፍል በሱስ ተጠቂቱ ከፍተኛ ቁጥር ይይዛል ተብሏል።

‎በተጨማሪም ሚኒስቴር መስራያ ቤቱ የአዕምሮ ጤና ሕክምናን በሁሉም የግልና የመንግሥት ተቋማት ለማስፋት ብሎም ግንዛቤ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

‎ይህም እንደሀገር በጤናው ዘርፍ፣ በኢኮኖሚው እና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ተብሏል።

‎ሱስ ታክሞ የሚድን የጤና ቀውስ በመሆኑ በሱስ የተጠቁ ግለሰቦችን ከሱስ እንዲወጡ ማድረግ መንከባከብ የሁሉም ሰው ሀላፊነት ሊሆን እንደሚገባ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናውን የሰጡ የዘርፉ ባለሞያዎች አሳስበዋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ