ሐምሌ 2/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የነዳጅ አቅርቦት እጥረት በመኖሩ በትራንስፖርት ስምሪት አገልግሎቱ ላይ ትልቅ ፈተና መሆኑ የክልሉ ትራንስፖርትና የመንገድ ልማት ቢሮ ለአሐዱ አስታውቋል። ‎

የክልሉ ትራንስፖርትና የመንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዘውዴ ተፈራ ሰሞኑን በክልሉ በአንዳንድ ከተሞች ነዳጅ ለመቅዳት የሚታይ ረጃጅም ሰልፍ መኖሩን የገለጹ ሲሆን፤ "በዚህም በትራንስፖርት ስምሪት አገልግሎቱ ላይ ትልቅ ፈተና ሆኗል" ብለዋል።

‎ዳይሬክተሩ አያይዘውም በክልሉ በበጀት ዓመቱ 557/2016 በተቀመጠው አዋጅ መሰረት በማድረግ ደንብን ተላልፈው የተገኙ 108 ሺሕ 655 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል። ‎በዚህም አሽከርካሪዎች ላይ በተደረገ የገንዘብ ቅጣት ከ113 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት ገቢ መደረጉን ለአሐዱ ገልጸዋል።

Post image

በክልሉ በ2ዐ17 ዓ.ም አጠቃላይ የተመዘገቡ የትራፊክ አደጋዎች 453 ሲሆኑ፤ ከእነዚህም መካከል 180 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ. ከባድ የአካል ጉዳት 197 76 የሚሆን ደግሞ ቀላል አደጋ ሆነው መመዝገባቸውን አስረድተዋል፡፡

‎በተጨማሪም በትራፊክ አደጋ ምክንያት በንብረት ላይ የደረሰው ውድመት ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የክልሉ ትራንስፖርትና የመንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዘውዴ ተፈራ አብራርተዋል።

‎"በበጀት ዓመቱ የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ አንፃር ከ2016 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር 2 በመቶ መቀነስ ተችሏል" ያሉት ዳይሬክተሩ ፤የትራንስፖርት አገልግልትን ፍትሐዊ ለማድረግ እና የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ብዙ ጥረቶች ቢደረግም አሁንም ክፍተቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

‎የትራፊክ አደጋን ለመቀነስና ለመከላከል የሁሉም ህብረተሰብ ተሳትፎ እና ኃላፊነት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ