‎ጥቅምት 6/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) በአክሱም ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት ትናንት ጥቅምት 5 ቀን 2018 ከሰአት 7:30 ገደማ የእሳት ቃጠሎ አደጋ መከሰቱ ተገልጿል፡፡

በእሳት ቃጠሎው በሆስፒታሉ የሚገኝ ዋና መድኃኒት መጋዝን ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፤ በውስጥ የነበሩ በሚልዮኖች የሚገመቱ የሕክምና መሳርያዎችና ግብዓቶች መውደማቸው ተነግሯል፡፡

Post image

እሳት አደጋውን የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች፣ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች፣ የአክሱም ከተማ ፀጥታ አባላት፣ የአክሱም ከተማ ማዛጋጃ ቤት፣ የአክሱም ከተማ ወጣቶች፣ ፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እሳት አደጋ ሠራተኞች በጋር በመሆን ተቆጣጥረውታልም ነው የተባለው።

የአደጋው መንሰኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝም የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስታውቋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ