መስከረም 13/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያ ወረዳ 59 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

በዛሬው ዕለት መነሻውን ከመካነ ሰላም ያደረገ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ደሴ ዙሪያ ወረዳ ቀበሌ 015 ልዩ ቦታው "ዳባ መግለቢያ" አካባቢ የተገለበጠ ሲሆን፤ በአደጋው 49 ሰው ከባድና ቀላል ጉዳት ሲደርስባቸው እሰካሁን 12 ሰው ሕይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።

Post image

አደጋውን ተከትሎ የወረዳው የፀጥታ አካላት አንቡላንስና ክሬን በመያዝ በቦታው ላይ ተገኝተው፤ ተጐጂዎችን ወደ ሆስፒታል እያደረሱ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ፖሊስ የአደጋው መንሰኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡