ሐምሌ 1/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ ከበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 ትምህርት ዘመን የነባር እና የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ሐምሌ 01/2017 ዓ.ም እንደሚጀመር የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በዚህ መሠረት በትምህርት ቢሮው ሥር ባሉ የመንግሥት፣ የግል እና በሌሎች የተያዙ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2018 ትምህርት ዘመን የትምህርት ቀናት መቁጠሪያ (የትምህርት ካላንደር) ካላንደርን ይፋ ተደርጓል፡፡

Post imagePost image

በዚህም የ2018 ትምህርት ዘመን የነባር እና የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 01 እስከ ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ካላንደሩ አመላክቷል።

እንዲሁም የ2018 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ቀን መደበኛ ትምህርት መስከረም 05/2018 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ