መስከረም 28/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 እየተሰራ ባለው የአፍንጮ በር የወንዝ ዳርቻ ልማት በካይ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቀን የንግድ ተቋም (ጠጅ ቤት) 300 ሺሕ ብር መቅጣቱን አስታውቋል።

የተወሰደውን እርምጃ አስመልክቶ የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ ዋና ሳጅን ውባለም ሽፈራው እንደገለፁት፤ ድርጅቱ በተደጋጋሚ ወደ ወንዝ የሚለቀውን በካይ የፍሳሽ ቆሻሻ እንዲያቆም ግንዛቤ ቢፈጠርለትም ከድርጊቱ መቆጠብ ባለመቻሉ ከክፍለ ከተማው የአካባቢ ጥበቃ ፅ/ቤት ጋር በመሆን የቅጣት እርምጃ ተወስዶበታል።

Post image

ባለስልጣኑ መሰል ደንብ መተላለፎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ገልጸው፤ ደንብ ተላላፊዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ድርሻ በመሆኑ ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማዎች 9995 ነፃ የስልክ መስመእንዲጠቀሙ ጥሪውን አቅርቧል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ