ጥቅምት 18/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤቱ አባላት በቀረቡላቸው ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሞላጎ ደል አጀንዳ መሰብሰቡን ገልጸዋል።
ምክክሩ "ይበጃል" በሚል በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ሌሎች አካባቢዎች ዜጎች ተሳታፊ መሆናቸውን አንስተው፤ "አይበጅም" ያሉት በበኩላቸው አለመሳተፋቸውን ገልጸዋል፡፡ አክለውም "ሁሉም ሰው ውይይት አይፈልግም" ብለዋል።
በውጭ ሀገራትም የአጀንዳ ማሰባሰብ መደረጉን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለንደን በተደረገው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት "ጥቂት ኢትዮጵያውያን በርካታ ኤርትራውያን ምክክር አያስፈልግም ብለው ሰልፍ ወጥተው ነበር" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
"ኤርትራውያን በእኛ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው ሰልፍ መውጣታቸው ጥሩ ቢሆንም፤ ንግግሩን ግን በናንተ ቤት ብትጀምሩት ጥሩ ነው። የእኛን ሰልፍ ከማጀብ የእናንተን ቤት ብትመለከቱ ይሻላል" ሲሉም መልዕክት አስተላፈዋል።
ይህን አይነት ሁነቶች በየቦታው ተመሳሳይ ሙከራዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
እንዲሁም የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ አስፈላጊ ነው በማለት በርካታ ሀሳቦች ተሰጥጠውበት አጀንዳ መገኘቱን ጠቁመዋል።
"ሀገራዊ ምክክሩ ያለን ስርዓት የሚያፈርስ ሳይሆን የሚገነባ ነው። ምርጫን የሚያስቆም በጀት የሚያስቆም የወታደር እንቅስቃሴ የሚያስቆም ምክክር አንፈልግም። መንግሥት እንደ መንግሥት እየሰራ ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች ይመጣሉ እንጂ መንግሥት ወራውን ያቆማል ማለት አይደለም። ከምርጫ ጋር አይገናኝም ምርጫን የሚረብሽ ነገር ያለ አይመስለኝም" ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
"በለንደን በተደረገው አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ኤርትራውያን 'ምክክሩ አያስፈልግም ብለው' ለተቃውሞ ወጥተዋል" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
"ንግግሩን ግን በራሳቹ ቤት ብትሞክሩት ይሻላል" ሲሉም ገልጸዋል