ሰኔ 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግሥትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፤
👉 የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ በመሆኑን ተከትሎ፤ የጤና ባለሙያዎች፣ መምህራንና በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ፡፡የመንግሥት ሠራተኞችን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል አኳያ የመንግሥት ምላሽ ምንድነው?
👉 የሥራ አጥነት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ የተያዙ አቅጣጫዎች ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጥ?
👉 መንግሥት የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠትና በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ በከተሞች የታየውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ምን እየሰራ ይገኛል?
👉 ከውጭ ጠላቶች ጋር ግንባር ፈጥረው የሚሰሩ ኃይሎችን ከማጋለጥ ረገድ በመንግሥት በኩል ምን እየተሰራ ነው?
👉 በሕወሓት የጦርነት ናፍቆትና ጸብ አጫሪነት ምክንያት ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል። በትግራይ ክልል ያለው አሁናዊ የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ ምን ይመስላል?
👉 ሀገራዊ ምክክር በትግራይ ክልል በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ እንዲሁም እንደ ሀገር ኢትዮጵያውያን የሚመኙትን ውጤት እንዲያመጣ ከማን ምን ይጠበቃል?
👉 መንግሥት "ካለፉት ጊዜት በአንጻራዊነት የተሻለ ሰላም እያመጣን ነው" ይላል ማሳያዎቹ ምንድን ናቸው?
👉 በተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ታዳጊዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ምን እየተሰራ ይገኛል?
👉 ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ እቅድ አፈጻጸም ከቁልፍ የኢኮኖሚ እድገት አመላካቾች አንጻር በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ማብራያ ቢሰጥ? የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች ይገኙበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ