መስከረም 15/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) ነዋሪነታቸውን በሸገር ከተማ ለገዳዲ ከተማ ያደረጉት ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ ሜሮን ስዩም አጋ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የ'በሸ ጥቅል' አራተኛ ዙር የአንድ ሚሊዮን ብር አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ወ /ሮ ሜሮን ስዩም "የኑሮ ውድነቱ ከአቅሜ በላይ ሆኖብኝ ወደ አረብ ሀገር ሄጄ በሰው ቤት ተቀጥሬ እየሰራሁ ገንዘብ እየላኩ ልጆቼን ለማሳደግ በእቅድ ላይ ብሆንም፤ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የአንድ ሚሊዮን ብር የ'በሸ ጥቅል' አሸናፊ እንደሆንኩ ሳውቅ፤ ስደቱንም ሰርዠዋለሁ" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

የዕድሉ አሸናፊ ለመሆን ያበቃቸውንም ሁኔታ ሲያስረዱ፣ "የሳፋሪኮሞ ኢትዮጵያ በየቀኑ የበሸ ጥቅል የ25 ብር ካርድ ለአራት ወራት ያህል ስሞላ በመቆየቴ ነው" ብለዋል።

Post image

"አሸናፊ በመሆኔ ደስታዬ ወደረ የለውም" ያሉት ወ/ሮ ሜሮን ስዩም፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያንም ይህን እድል በማመቻቸት ተጠቃሚ ስላደረጋቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያም በአራተኛ ዙር የበሸ ጥቅል አሸናፊ ለሆኑት ወ/ሮ ሚሮን ስዩም፤ የአንድ ሚሊዮኑን ብሩን በዛሬው ዕለት ማስረከቡን ለአሐዱ አስታውቋል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሪጅናል አኪውዚሽን ማናጀር የሆኑት አቶ ኦብሳ ደጀኔ፤ ተቋሙ ተደራሽነቱን በማስፋት ለደንበኞች ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ የበሸ ጥቅል ተጠቃሚ ዘመቻን ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ሙዝየም በይፋ ማስጀመሩ ይታወሳል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ