ጥቅምት 6/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የፓኪስታን ንግድ ልማት ባለስልጣን (TDAP) እና የፓኪስታን ንግድ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የፓኪስታን ኤምባሲ የንግድ ክፍል ጋር በመተባበር ያዘጋጀአምስተኛውን የፓኪስታን አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤ እና የፓኪስታን ምርቶች ኤግዚቢሽን በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

በአዲስ አበባ ሚሊንየም አዳራሽ የተከፈተው ኤግዚቢሽን ጥቅምት 6 እስከ 8 2018 ዓ.ም. ድረስ ይካሄዳል።
አውደርእዩ በፓኪስታን እና በአፍሪካ መካከል የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎችን በመፍጠር የተዘጋጀ ሲሆን፤ በጉባኤው የአፍሪካና የፓኪስታን ከፍተኛ የመንግሥት ልዑካን፣ የንግድ መሪዎች፣ ባለሀብቶችና ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

ከ100 በላይ የፓኪስታን ኩባንያዎች የተለያዩ ምርቶችና አገልግሎቶቻቸውን ይዘው ቀርበዋል።
ከምርቶቹ መካከል መድኃኒቶች፣ የሕክምና መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ ምግብ ነክ ምርቶች፣ የውበት መጠበቂያዎች ይገኙበታል፡፡
በአውደ ርዕዩ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ የፓኪስታን ንግድ ሚኒስቴርን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ሲገኙ፤ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር የትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ኃላፊዎች በአካል ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
ጉባኤው ከዚህ ቀደም በደቡብ አፍሪካ፣ በናይጄሪያ እና ኬንያ ተከናውኗል።

ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የንግድ ትስስር ለማጠናከር በማሰብም 5ኛውን ዙር በኢትዮጵያ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ