መስከረም 19/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺሕ 136 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 10 ዙር በረራ ወደሀገራቸው የተመለሱት 1 ሺሕ 306 ወንዶች፣ 749 ሴቶች እንዲሁም 81 ጨቅላ ሕጻናት መሆናቸው ተገልጿል።
ከተመላሾች መካከል 354 ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆነቸውንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በተያዘው ዓመት መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ እስካሁን 3 ሺሕ 682 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉንም የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገልጿል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ