ጥቅምት 3/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) 18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በዛሬው ዕለት በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ሁነቶች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
ቀኑ "ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ" በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚከበረው፡፡
የብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በሠንደቅ ዓላማ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 863/2006 (እንደተሻሻለው) አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ መጀመሪያ ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ተደንግጓል።
በዚህም መሠረት ቀኑ የፌደራል የመንግሥት ተቋማት፣ የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች፣ የመከላከያ ሰራዊት ካምፖች እንዲሁም ኤምባሲዎችና የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች በተመሳሳይ ሰዓት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ሠንደቅ ዓላማ በመስቀልና በሠንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ በመፈፀም እንዲሁም በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረውታል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በመከበር ላይ ነው
